☕️ Announcements

1. Koshe Renewal Program Center: A church program designed to bring about fundamental and practical life change in Koshe and the surrounding community, especially the youth through the Gospel. The center is being established by the church and we had asked 300,700.00 to carry out a life-changing discipleship training program and biblical life skills training through the ministry of the saints and we want to give thanks as the budget has been closed.

2. Beza Family Day 2024: We will be having a Beza Family Day on May 28 starting from 9am at the Cambridge School! It will be a full day program where we will have a time of fellowship and fun with different games that bring together people of all ages. So, if you want to participate in the program you can register at the connection center from next week.

3. Beza Kidz: We will have a Sunday School program provided for children during the Joint Fasika/Easter service on May 5th after worship. Kids will be dismissed together from the main sanctuary.

4. Our International Community Fellowship (ICF): is having a Meet and Greet fellowship meeting to allow people in the international community feel welcome and want to encourage those who have never joined us to come to the meeting on May 4 at 10am at a home. Please contact brother James 0900807888. Come and fellowship with us!

5. Fasting and prayer: We will be having our regular Beza 3-day fasting and prayer program here at the Beza Tabernacle starting from Tuesday April 30-  May 2 from 10 am to 6 pm. Please mark your calendar and let us come together as a body to seek the face of the Lord!

6. Easter Sunday Joint Service: May 5 is the Ethiopian Easter Sunday. We will be having a joint service at 10am in the morning for both services. So, please come at 10am and not at the usual time. We will have a time of worship and celebration of the resurrection of Christ. Invite family and friends!

7. Good Friday Worship Night (Amharic Only): We will be having a Worship Night on May 3 Ethiopian Good Friday at 5pm at the tabernacle. We will be having a message on the work of the cross so please invite someone who needs to hear the message. Pray for who the Lord will have you bring that day. Invite one person who needs to hear the message!

8. Beza Youth Discipleship Class: will launch a unique Beza Youth discipleship class for youth ages 14 to 19. Register at a connection center if you're not baptized and would like to participate in a 4-month discipleship program led by teachers who can engage with young people. The starting day of the class is May 12, 2024. Class Time: 11 a.m. to 1 p.m.

HomeCare: Our small groups meet all over the city during the week and it is where we make friends, be discipled, make disciples. Homecares are where we learn to follow Jesus, through diligent study of God’s word and intentional fellowship with other believers. We invite you to get settled in these intimate and fun settings where you can plug in to Christian community. To join a homecare near you, Please register by texting the Beza phone 0907700007 or call 0920732414 or send a message through our telegram handle @Bezaconnect.

Worship Schedule: worship schedule for our Sunday services:

Amharic service: 8:45 AM - 10:45 AM

English service: 11:15 AM to 1:15 PM

Children’s programs:

Ages 3 – 11 – begins at 11:45 AM

Ages 12 – 14 – begins at 11:45 AM

English High schoolers- begins at 11:45 AM

Discipleship classes: Discipleship classes will be held every Sunday in our classes here at the Tabernacle on 10:00 AM to 11:00 AM.

Prayer Unusual is a going strong. The prayer movement that started at Beza Church is a program where we come and intercede for the nation and for our personal needs. It is being held at the hall dedicated in the basement of the new building for prayer.

Schedule for Prayer Unusual:

Thursday 3 – 5 PM

Friday 1:00PM- 3:00PM Women’s Fellowship

Friday 4 – 7PM (English Program)

Saturday 7 – 8AM Online via Telegram click JOIN on the top of our Telegram Channel (@bezachurch) and join the prayer.

Sunday 7:30 – 8:30AM

☕️ ማስታወቂያ

1. ቆሼ ተሀድሶ ፕሮግራም ማዕከል:- በቆሼና በአካባቢው በማህበረሰቡ ዘንድ በተለይ በወጣቱ የሕብረተሰብ ክፍል በወንጌል አማካይነት በመንፈሳዊና በአስተሳሰብ መረሰረታዊና ተጨባጭ የሕይወት ለውጥ ለማምጣት የተቀረፀ የቤተክርስቲያን ፕሮግራም ነው፡፡ ማዕከሉ በቤተክርቲያን የተቋቋመ ሲሆን በቅዱሳን አገልግሎት የወንጌል ስርጭትና ሕይወት ለዋጭ የሆነ የደቀመዝሙር ትምህርት አገልግሎት እና መጽሐፍ ቅዱሳዊ የሕይወት ክህሎት ስልጠና ለማካሄድ ብር 300,700.00 ጠይቀን በጀቱ ሙሉ በሙሉ ስለሞላ ተባረኩ!

2. የቤዛ ቤተሰብ ቀን 2016: ግንቦት 20 የቤዛ ቤተሰብ ቀን ከጠዋት 3 ሰአት ጀምሮ በካምብሪጅ ት/ቤት ይኖረናል! የሙሉ ቀን ፕሮግራም ሲሆን በዚያም በሁሉም የዕድሜ ክልል ውስጥ የሚገኙ ሰዎችን የሚያሳትፍ የሕብረትና የመዝናኛ ጊዜ ይኖረናል። ስለሆነም በፕሮግራሙ ላይ መሳተፍ የምትፈልጉ ሁሉ ከሚቀጥለው ሳምንት ጀምሮ በመገናኛ ማዕከሉ መመዝገብ ትችላላችሁ።

3. ቤዛ ኪድዝ: ሚያዚያ 27 ከፋሲካ የጋራ አምልኮ በኋላ ለህፃናት የተዘጋጀ የሰንበት ትምህርት ቤት ፕሮግራም ይኖረናል። ስለሆነም ከአምልኮ በኃላ ልጆች ወደ ክፍላቸው ይሄዳሉ።

4. የቤዛ ጾም ፀሎት: እዚሁ ቤዛ ታበርናክል ማክሰኞ ከሚያዚያ 22 - 24 ከጠዋቱ 4 ሰዓት እስከ ምሽቱ 12 ሰዓት መደበኛ የ3 ቀን የጾም ፀሎት ፕሮግራም ይኖረናል። እባካችሁ ቀኑን መዝግቡት እና የጌታን ፊት ለመፈለግ እንደ አካል እንሰባሰብ!

5. የትንሳኤ ሰንበት አገልግሎት: ሚያዝያ 27 የትንሳኤ ሰንበት ነው። ለሁለቱም አገልግሎቶች ከጠዋቱ 4 ሰዓት ላይ የጋራ የአምልኮ ጊዜ ስለሚኖረን በተለመደው ሰዓት ሳይሆን በ4፡00 ላይ ኑ። ቤተሰብና ጓደኞች ይጋብዙ!

6. የስቅለተ ዓርብ የአምልኮ ምሽት: ሚያዝያ 25 ስቅለተ ዓርብ ከቀኑ 11 ሰዓት ጀምሮ በታበርናክል የአምልኮ ምሽት ይኖረናል። ስለ መስቀሉ ሥራ የወንጌል መልዕክት ስለሚነገር መልዕክቱን መስማት ያለበትን ሰው ጋብዙ። ያን ቀን ማንን መጋበዝ እንዳለባችሁ ጌታ እንዲያሳያችሁ ፀልዩ። መልዕክቱን መስማት ያለበትን አንድ ሰው ጋብዙ!

7. የቤዛ የወጣቶች ደቀመዝሙርነት ክፍል:  ከ14 እስከ 19 አመት ለሆኑ ወጣቶች ልዩ የሆነ የቤዛ የወጣቶች ደቀመዝሙርነት ትምህርት ክፍል እየመዘገብን ነው።  ለወጣቶች በተዘጋጀ የ4 ወር የደቀመዝሙርነት ፕሮግራም ላይ መሳተፍ ለምትፈልጉ ወጣቶች እባካችሁ በመገናኛ ማዕከሉ ተመዝገቡ። ትምህርቱ የሚጀመረው እሁድ ግንቦት 4/2016 ሲሆን ከጠዋቱ 5 ሰዓት እስከ 7 ሰዓት ነው።

ሆምኬር፡- የቤት ውስጥ ሕብረቶቻችን በሳምንቱ ውስጥ በመላ ከተማው ይሰበሰባሉ። እነዚህ ሕብረቶች ወዳጆች የምናፈራበት፣ የምንማከርበትና ደቀ መዛሙርት የምንሆንባቸው ናቸው። ሆምኬሮች የእግዚአብሔርን ቃል በትጋት በማጥናትና ከሌሎች አማኞች ጋር በመተባበር ኢየሱስን መከተል የምንማርበት ነው። ከክርስቲያን ማህበረሰብ ጋር በምትገናኙባቸው በእነዚህ ቅርበት የተሞላባቸውና አስደሳች ሕብረቶች ውስጥ እንድትተከሉ እንጋብዛችኋለን። በአቅራቢያዎ ወደሚገኝ ሆምኬር ለመቀላቀል በቤዛ ስልክ ቁጥር 0907700007 ወይም በ0920732414 ይደውሉ ወይም በቴሌግራም አድራሻችን @Bezaconnect መልእክት በመላክ ይመዝገቡ።

የአምልኮ ሰዓት:- የእሁድ የአምልኮ ሰዓት፦

የአማርኛ አገልግሎት፦ ከ 2:45 - 4:45

የእንግሊዝኛ አገልግሎት፦ ከ 5:15 - 7:15

የልጆች የሰንበት ትምህርት ፕሮግራም ማስተካከያ፦

ዕድሜያቸው 3 እስከ 11 - በ3:15 ሰዓት ይጀምራል

ዕድሜያቸው 12 እስከ 14 እድሜ - በ2፡45 ሰዓት ይጀምራል

የወጣቶች ፕሮግራም:- የቤዛ የወጣቶች ፕሮግራም ዕድሜያቸው ከ 15-23 ለሆኑ በየሳምንቱ እሁድ በአዲሱ ሕንጻ ቤዝመንት ከ2፡45-4፡45 ይካሄዳል። በየወሩ ከጠዋቱ 3፡00 እስከ 5፡00 የሙሉ ቀን ፕሮግራም ይኖረናል።

የደቀመዝሙርነት ትምህርት:- የደቀመዝሙርነት ትምህርት እሁድ በታበርናክል ከጠዋቱ 4፡45 እስከ 5፡45 ሰዓት ይካሄዳል። እሁድ መውሰድ የማይችል ማንም ሰው የደቀመዝሙርነት ትምህርት መውሰድ ከፈለገ በሌሎቹ ቀናት ፕሮግራም ስለምናዘጋጅ የምትፈልጉ እባካችሁ በዚህ ቁጥር "0907700007" አጭር የጽሑፍ መልክት በመላክ ወይም በዚህ የቴሌግራም አድራሻ "@bezaconnect" ይመዝገቡ።

ያልተለመደ ፀሎት ላለፈው ወር በርትቶ እየቀጠለ ነው። በቤዛ ቤተክርስቲያን የተጀመረው የፀሎት እንቅስቃሴ በየሳምንቱ እየቀጠለ ስለሆነ ይምጡና ለሃገራችንና ለተለያዩ ጉዳዮች ማልዱ። በአዲሱ ህንፃ ምድር ቤት ለፀሎት በተዘጋጀው አዳራሽ ውስጥ እየተካሄደ ነው።

ያልተለመደ ፀሎት መርሃ-ግብር፦

ሐሙስ - ክቀኑ 9፡00- 11:00 ሰዓት

ዓርብ - ከቀኑ 7:00- 9:00 ሰዓት (የእህቶች ፕሮግራም)

ዓርብ - ከቀኑ 10 ሰዓት - ምሽቱ 1 ሰዓት (የእንግሊዘኛ ፕሮግራም)

ቅዳሜ ከጠዋቱ 1 ሰዓት-2 ሰዓት በቴሌግራም (ለመግባት በቴሌግራም ቻናላችን (@bezachurch) ከላይ JOIN የሚለውን በመጫን በቀላሉ ፀሎቱን መቀላቀል ትችላላችሁ።)

እሁድ - ከጠዋቱ 1:30 ሰዓት – 2:30 ሰዓት